
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ
21 October 2025 – It is with great sorrow that the Crown Council of Ethiopia marks the passing of Grand Mufti Haji Umer Idris, the former President of the Supreme Council of Islamic Affairs in Ethiopia. Known widely as “Haji Mufti” he was very deeply revered not just in the Muslim community, but across all faiths in Ethiopia. This fact is underlined by the vast crowds of people of every faith who paid their respects to him yesterday at his funeral. Grand Mufti Haji Umer Idris was a voice for love, unity, morality, mutual respect, good neighborliness, and patriotism. He displayed the very essence of what it meant to be a good Ethiopian, and a person of faith. His wisdom, wit, and kindness will be deeply missed by all. We join with all people of faith in our country in mourning this deeply holy man. We extend our sincere condolences to his family, to the Muslim community, and share the grief of the entire Ethiopian people at the loss of a national elder. May he rest in peace.
Prince Ermias Sahle Selassie Haile Selassie, President of the Crown Council of Ethiopia
የኢትዮጵያ ዘውድ ምክር ቤት የታላቁን አባት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የነበሩት የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ዜና እረፍት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን ልንገልጽ እንወዳለን። “ሐጂ ሙፍቲ” ተብለው የሚታወቁትና ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ ከበሬታ ያተረፉት ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ከሁሎም ቤተ እምነት ተከታይዎች ነው። ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ለፍቅር፥ ለአንድነት፥ ለሥነ ምግባር፥ ለመከባበር፥ ለጥሩ ጎረቤትነት፥ ለሀገር ወዳድነት ድምጽ ነበሩ። የጥሩ ኢትዮጵያዊነት እና የጥሩ አማኝነት ምሳሌ ነበሩ። በሳልነታቸው፥ ጥበባዊነታቸው፥ እና ደግነታቸው መቼም አይረሳም። መጽናናትን ለቤተሰባቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ እንመኛለን። ከመላው የአገራችን ሕዝብ ጋር የእኚህ ታላቅ የአገር ሽማግሌ መለየት ምክንያት በደረሰብን ሐዘን ተካፋዮች መሆናችንን እንገልጻለን። ፈጣሪ ነፍሳቸውን ያሳርፍልን።
ልዑል ኤርምያስ ሣሕለ ሥላሴ የዘውድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት።