
The Registry of Armorial Bearings and Badges Granted by The Ethiopian Crown Honours Office
Under the Authority of
የኢትዮጵያ ዘውድ ምክርቤት
The Crown Council of Ethiopia

Grantee
Mark Aaron Murawski, Jerusalem Officer of Honour
Blazon
Argent, a chevron Sable with five bezants, in base an anchor of the second, on a Traditional Ethiopian Round Shield ensigned with an Anfarro proper, flying therefrom to sinister 3 pennons Vert, Or, and Gules.
እነሆ፤ የኢትዮጵያ ዘውድ የክብር እውቅና ቢሮ አባል የሆኑት፤ ክቡርነታቸው ማርክ ሙራውስኪ፤ የእየሩሳሌም የክብር መኮንንና የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ የኮማንደር ማዕረግ ያላቸው፤ የጋሻ የክብር አርማ ከኢትዮጵያ ዘውድ የክብር እውቅና ቢሮ እንዲሰጣቸው ጥቅምት 22 ቀን 2015 ዓ.ም በማመልከታቸው፤ ስለሆነም፤ ይህ ይታዎቅ፤ እኛ የኢትዮጵያ ዘውድ የክብር እውቅና ቢሮ፤ የአመልካቹን ጥያቄ ተቀብለንና ደግፈን፤ ለልጆቻቸውና ለልጅልጆቻቸው መተላለፍ የሚችለውን የክብር ጋሻ አርማ በዚህ በኢትዮጵያ ዘውድ የክብር እውቅና ቢሮ በተሰጠ ህጋዊ ሰነድ እናረጋግጣለን፡፡ ስለዚህም ስጦታችን በመዝገባችን ውስጥ በቁጥር IN004 የሚከተለውን ጨምረን መዝግበናል፡ ወደ ታች የተገለበጠ የቪ ምልከት ባለው ጥቁር ጨርቅ ላይ፤ አምስት ወርቃማ ክብ ኳሶች፤ ክብ በሆነና ወርቃማ መሰርት ባለው የኢትዮጵያ ባህላዊ ጋሻ ላይ ተቀምጠው ይታያሉ፡፡ የመርከብ ማሰሪያ ብረት ደግሞ ከኳሶች በታች በጋሻው ላይ ተቀምጧል፡፡ ከጋሻው በታች፤ የአንገት ሪባንና የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ የኮማንደር ማዕረግ ኒሻን ተንጠልጥለዋል፡፡ በጋሻው ላይ ከተቀመጠው አንፋሮ ጋር በቀኝ በኩል የተየያዙ አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ቀለም ያላቸው ሪባኖች ወደቀኝ ይውለበለባሉ፡፡
Registration Information
№ IN004
1 January 2025 / 23 ታኅሣሥ 2017
Emblazonment
Jericho Officer of Honour
Recipient Type
Individual
Other Information
Designed by Jerusalem Officer of Honour
* This Registry is intended for research purposes only. The heraldic emblazonments found herein may not be reproduced in any form or in any media without the written consent of The Ethiopian Crown Honours Office and/or the Armiger.