Skip to content

Statement on the Passing of Lij Kidane Wold Alemayehu

October 19, 1936 – March 22, 2026 / ጥቅምት ፱ ፡ ፲፱፻፳፱ – መጋቢት ፲፫ ፡ ፳፻፲፰ 

The Crown Council of Ethiopia expresses its great sorrow at the passing of Lij Kidane Wold Alemayehu. We hereby convey our sincere condolences to his widow Woizero Amasale Hailu, to his children, grandchildren, extended family, and loved ones.

Lij Kidane tirelessly served his country and his people from his youth up to the end of his life. Before leaving his country, he worked in the Ministries of Education and the Interior for 12 years. He then worked with the Imperial Telecommunications Board in several high-level posts and was awarded the Order of the Star of Honour of Ethiopia by His Imperial Majesty Emperor Haile Selassie I for his service. After this, Lij Kidane worked with United Nations agencies for 28 years, in key developmental roles, in eleven different African and Middle Eastern countries.

After his retirement, Lij Kidane sought to address some unresolved issues of justice in Ethiopia. Among his efforts was his relentless campaign seeking an official apology and compensation from the Italian government and the Vatican for the atrocities committed against Ethiopia during the fascist invasion and occupation. He founded and led the international organization known as “The Global Alliance of Justice – The Ethiopian Cause,” thus showing his dedication to the cause of justice for Ethiopia and Ethiopians.

Lij Kidane was a very humble, respectful person, clothed in the mannerliness of a good Ethiopian. He strove tirelessly for his country.

May God repose the soul of Lij Kidane and comfort his family and loved ones.


የልጅ ኪዳነ ወልድ አለማየሁን ህልፈተ ሕይወት አስመልክቶ የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን በዘውድ ምክር

ቤት ስም ለመግለጽ እንወዳለን። ለሚስታቸው ለወ/ሮ አምሳለ ሀይሉ፣ ለልጆቻቸውና የልጅ ልጆች እንዲሁም ለዘመድ አዝማድና ወገኖቻቸው ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን።

ልጅ ኪዳኔ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ከወጣትነታቸው ጊዜ ጀምሮ ተግቶ በመስራት ሀገርና ወገኑን በታማኝነት አገልግለዋል። ከሀገራችን ሳይወጡ በፊት ለአስራ ሁለት ዓመታት ያህል በትምህርትና የሃገር ግዛት ሚኒስቴር ውስጥ ሰርቷል። ከዚያም በመቀጠል በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ቴሌኮሙኒኬሽን ቦርድ በተለያየ ከፍተኛ የስልጣን እርከኖች ላይ በብቃት በማገልገላቸው በአጼ ኃይለ ሥላሴ “የኢትዮጵያ ክብር ኮኮብ” የተሰኘውን ሊሻን ማዕረግ ተሸልመዋል። ከዚያም በኋላ ለሃያ ስምንት ዓመታት በተባበሩት መንግሥታት በአፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ በአስራ አንድ የተለያዩ ሀገሮች ውስጥ ወሳኝ በሆኑ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ላይ በከፍተኛ ሃላፊነት ላይ ሆኖ ሰርተዋል። በጡረታ ዕድሜያቸው በሀገራችን ያልተቋጩ የፍትሕ ጥያቄዎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው፣ ልጅ ኪዳኔ ባላቸው ዕውቀትና ችሎታ ለውጥ ለማምጣት የበኩላቸውን ድርሻ በሚገባ ተወጥተዋል። ከበርካታ ስራዎቻቸው አንዱ የዛሬ ዘጠና አንድ ዓመት በፊት የቀድሞ ፋሺስት ኢጣላያን መንግሥት ቫቲካንን ተገን አርጎ የቦምብ መርዝ በመጠቀም በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያን ላይ ላደረሱት ዕልቂት፣ የጦር ወንጀሎች እንዲሁም የቅርስና የንብረት ማውደምና ማጥፋት ይቅርታ እንዲጠይቁና ተገቢውን ካሳ እንዲከፍሉ The Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause የተሰኘውን ዓለም አቀፋዊ ድርጅት በመምራት ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ፍትሕ ቋሚና ተሰላፊነታቸውን በመመስከር እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ የዜግነት ድርሻቸውን በሚገባ ተወጥተዋል።

ልጅ ኪዳኔ በጣም ትሁት፣ ሰው አክባሪና ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን የተላበሱ ግሩም ሰው ነበሩ። ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለሀገራቸው የሚቻላቸውን ሁሉ አድርጓል።

የልጅ ኪዳኔን ነፍሥ እግዚአብሔር ይማር፣ ለቀሪውም ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድና ወዳጆች ሁሉ መጽናናትን ይስጥልን።